ጃፓኖች ከሰውና ከእንስሳት የተዳቀሉ የሰው አካላትን ለመፍጠር ሙከራ ላይ ናቸው

አዲስ የተወለዱ ጨቅላ አይጦች Image copyright Getty Images

የሰው ልጅ ለዘመናት ሰውንና እንስሳትን በማዳቀል አዲስ ፍጥረት የመፍጠር እሳቤዎች ነበሩት፤ ከነዚህም ውስጥ አንዱ በጥንታዊዋ ግሪክ ሰውና እንስሳትን በማዳቀል ለሚፈጠሩ ፍጡሮች ቺሜራ የሚል ስያሜ ሰጥተዋቸዋል።

የሳይንስና የቴክኖሎጂ ግኝቶች በላቁበት በዚህ ዘመን እነዚህ እሳቤዎች እውን ለመሆን ተቃርበዋል። በቅርቡም የጃፓን መንግሥት ለአንድ የሳይንቲስቶች ቡድን የሰው ልጅ አካላትን በእንስሳት ሽልና ማህፀን ውስጥ እንዲያድጉ ፍቃድ ሰጥቷል።

ሳይንቲስቱ መንትዮች ኤች አይ ቪ እንዳይዛቸው ዘረ መላቸውን አስተካከለ

የህጻናትን ዘረ መል ማስተካከል ክልክል ነው?

ምርምሩን የሚመሩት ሂሮምትሱ ናካውቺ ሲሆኑ ከቶክዮና ከስታንፎርድ ዩኒቨርሰቲዎች የተውጣጡ ተመራማሪዎችን ያሳተፈው ይህ ፕሮጀክት ለዚህ ሙከራ ተብለው በተዘጋጁ አይጦች ሽል ላይ የሰውን ህዋስ በመውጋት የሰው ልጅ ጣፊያ እንዲፈጠርና እንዲያድግ የሚደረግ ሙከራ ይከናወናል ተብሏል።

ሽሎቹም ካደጉ በኋላ በንቅለ ተከላ አማካኝነት ወደ ሌሎች እንስሶች ማህፀን እንዲገቡ ይደረጋል። የፕሮፌሰር ናኩቺም ዋነኛው አላማም የሰውን ልጅ አካላትን በእንስሳት ውስጥ መፍጠርና እነዚህንም አካሎች በንቅለ ተከላ አማካኝነት ወደ ሰው መግጠም (ማስገባት) መቻል ነው።

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ጃፓን የሰው ህዋስ የተወጉ የእንስሳት ሽሎች በዐሥራ አራት ቀናት ውስጥ እንዲቋረጡ ታደርግ ነበር፤ በእንስሳት ማህፀን ውስጥም እንዲያድጉ አትፈቅድም ነበር።

አሁን ያ እገዳው ተነስቶ ተመራማሪዎች ለፕሮጀክቶቻቸው ፍቃድ ማውጣት ይችላሉ ተብሏል።

Image copyright Getty Images

የሞራል ጥያቄዎች

የሰውና የእንስሳን ህዋስ ማዳቀል በሚደረጉ የምርምር ዘርፍ ላይ የፕሮፌሰር ናካውቺ የመጀመሪያ ሙከራ አይደለም፤ እሳቸውና ሌሎች ተመራማሪዎች ከዚህ ቀደም የሰው ልጅ ህዋስን በአይጥ፣ በአሳማና በበግ ሺሎች ላይ ማሳደግ ችለዋል።

የሳይንቲስቶቹ ዋነኛ አላማ እንደ ጣፊያ የመሳሰሉትን በከፍተኛ ደረጃ እጥረት የሚከሰትባቸው የሰው ልጅ አካላት በእንስሳት ውስጥ በመፍጠርና በማሳደግ ለንቅለ ተከላ ማዘጋጀት ነው።

''ለሴቶች ቦክስ ምን ያደርጋል እያሉ ያንቋሽሹናል''

ከሁለት ዓመታት በፊት ፕሮፌሰር ናካውቺ የስኳር ህመምተኛ አይጥ መፈወስ ችለዋል፤ ይህንንም ያደረጉት ጤነኛ የአይጥ ጣፊያን በአይጥ ሽል ውስጥ በማሳደግ ባደረጉት ንቅለ ተከላ ነው።

ነገር ግን እስካሁን ባለው ከሰው ልጅ ህዋስ ጋር የተገናኙ ሙከራዎች ህጋዊ ሁኔታዎችን ሳያሟሉ በመቅረታቸው እንዲሁም ሙከራዎቹ ሊሳኩ ባለመቻላቸው እውን ሳይሆን ቀርቷል።

ከዚህ በተጨማሪ ምርምሩ የሞራል ጥያቄዎችንም በማስነሳት ላይ ነው፤ ዋነኛውም አንገብጋቢ ጉዳይ የሰው ልጅ ህዋስን እንስሳት ውስጥ ካስገባነው በእንስሳት አእምሮ ውስጥ በመገኘት ልክ እንደሰው ልጅ አመዛዛኝ ሁኔታ ሊያላብሳቸው ይችላል የሚል ነው።

ነገር ግን ፕሮፌሰር ናካውቺ ሳይንሳዊ ሙከራው የሰው ልጅ ህዋሶች ወደ ጣፊያው ብቻ እንዲሄድ የሚያደርግ ስምምነት ላይ በመድረሳቸው ነው ከጃፓን መንግሥት ፍቃድ ያገኙት።

በሐምሌ ወርም ከጃፓን የትምህርት፣ ባህል፣ ስፖርትና ቴክኖሎጂ የተውጣጡ ልሂቃን የምርምር ሥራውን የተወሰኑ ነገሮችን አሟልቶና ሂደቱን ጠብቆ እስከሄደ ድረስ ቀጥልበት ብለውታል።

Image copyright Getty Images

'የሰው ፊት ያላቸው እንስሳት'

በአሁን ሰዓት እየተሞከረ ያለው በሳይንሳዊ መንገድ የሰውን ልጅ ጣፊያ እንዲያመርቱ ለማድረግ፤ በእንስሳት ሽል ላይ ጣፊያ የሚያመርተውን ዘረ መል ማቋረጥ ሲሆን ለወደፊት ደግሞ ጉበትና ኩላሊት የሚቀጥሉ ይሆናል ተብሏል።

ከዚያም የእንስሳቱን ሽል የሰው ልጅ ህዋስ ይወጉትና ሽሉ ሙሉ በሙሉ በራሱ እንዲያድግ ይተውታል። ከዚያም ሽል በእንስሳት ማህፀን ውስጥ እንዲገባ ይደረጋል።

ሚኒስቴሩ ለፕሮፌሰር ናካውቺ ፈቃድ የሰጠው ሙከራዎቹን በትንንሽ እንስሳት እንዲያካሂዱና በተቻለም መጠንም ዝርያቸው ከሰው ጋር የማይቀራረቡ መሆን አለባቸው በሚል እንደሆነ አያኮ ማሴዋ በጃፓን የብዝኃ ሕይወትና ደህንነት ዳይሬክተር ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ቡድኑ የሰው ልጅ ህዋሳትን የተሸከሙትን የእንስሶቹን ፅንስ አእምሮም በጥብቅ ይከታተላሉ ተብሏል። እንስሶቹ ከተወለዱም በኋላ ቁጥጥሩ ለሁለት ዓመታት የሚቀጥል ይሆናል ተብሏል።

በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት

ፕሮፌሰር ናካውቺ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ምርምራቸውን መስከረም ወር ላይ ይጀምራሉ።

በካሊፎርኒያ ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ በተደረገ ሳይንሳዊ ሙከራ ፕሮፌሰር ናካውቺ የሰው ልጅ ህዋስን ከበግ እንቁላል ጋር በማጣመር በበግ ሽል ውስጥ አድርገውት ነበር።

ከሃያ ስምንት ቀናት በኋላ ሽሉ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። ሽሉ በጣም ጥቂት የሰው ልጅ ህዋስ እንደያዘና ምንም ዓይነት የሰው ምልክትም እንደሌለው ፕሮፌሰር ናካውቺ ለአሻይ ሺምቡን ጋዜጣ ተናግረዋል።

"በበጓ ሰውነት ውስጥ ማደግ የቻሉት የሰው ልጅ ህዋሳት በጣም ጥቂት ናቸው፤ ምናልባትም ከሺዎች ወይም ከዐሥር ሺ ህዋሳት አንዱ ነው" በማለትም "በዚህ አካሄድ የሰው ፊት ያለው እንስሳ በጭራሽ ሊወለድ አይችልም" ብለዋል።

Image copyright Getty Images

የዝርያ ርቀት

የሰው ልጅ ህዋሳትን በሌላ ዝርያ ማሳደግ ቀላል አይደለም።

በቴክሳስ ዩኒቨርስቲ የሚገኙት ተመራማሪ ጁን ው እንደሚሉት ከሆነ ከሰውና ከእንስሳት የተዳቀሉ ሼሎችን ከሰው ልጅ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው እንደ አሳማና በግ ማህፀን ውስጥ ለማሳደግ መሞከር ምንም ትርጉም የለውም ይላሉ።

በነዚህ እንስሳት ውስጥ የሰው ልጅ ህዋስ የማደግ እድል የለውም ገና በሽል ውስጥ እያለ ይሞታል ብለውም ይከራከራሉ።

ባለፈው ወር የስፔን ሳይንቲስቶች ከሰውና ከዝንጀሮ የተዳቀለ ሽል በቻይና በሚገኝ ላብራቶሪ መፍጠራቸውን ስፓኒሽ ደይሊ ኤልፓይስ ዘግቦ ነበር።

ይህ ምርምርም ሲመራ የነበረው በፕሮፌሰር ጁዋን ካርሎስ ሲሆን ከዚህ ቀደምም ከሰውና አሳማ የተዳቀለ ሽል በላብራቶሪ ፈጥረዋል።

ተያያዥ ርዕሶች